+251-974-967171 | +251-936-177777
A.A, Bole Tropical Mall No. 217
Service Active Ethiopia Flag

International Tech Expo

ኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤትና በምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት

ኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤትና በምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት

Category: News

በተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ የተመራ የልዑካን ቡድን በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤትና በምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፍትህ አገልግሎት አሰጣጥን ዘመናዊና ውጤታማ ለማድረግ እየተሠራ ያለውን ማሻሻያ ጎብኝቷል።
በጉብኝቱ የተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ፣ ምክትል አፈ ጉባዔ፣ የተወካዮች ምክር ቤት የቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ የፌዴራል የጠቅላይና የከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንቶች፣ የፍትህ ሚኒስቴር፣ የክልል ምክር ቤቶች አፈ ጉባዔዎች፣ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንቶች፣ የክልሉ ፍትህ ቢሮ ኃላፊዎች፣ የምክር ቤቶች አስተዳደር እና የፍትህ ቢሮ ኃላፊዎች፣ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የፍትህ ቢሮ ኃላፊዎች እና፤ የፍርድ ሥርዓቱን ለማዘመን በሚደረጉ የቴክኖሎጂ መር ተግባራት መልከ ብዙ አሻራውን በማኖር ላይ የሚገኘው የስካይሊንክ ቴክኖሎጂስ ኃላፊ ተገኝተዋል።
"ጉብኝቱ ስካይሊንክ ቴክኖሎጂስ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እየሠራው በሚገኘው የስማርት ፍርድ ቤትና የአንድ መስኮት አገልግሎት አሰጣጥ ሂደት በርካታ ልምድ የተቀሰመበትና፤ በሌሎች ክልሎች ሊሠራቸዉ ለሚችለው የስማርት ፍርድ ቤቶች ተጨማሪ ግብዓቶች የተገኘበት ነበር" ሲሉ የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሙሐመድከረም አህመድ ገለፀዋል።

Subscribe for our latest update