+251-974-967171 | +251-936-177777
A.A, Bole Tropical Mall No. 217
Service Active Ethiopia Flag

International Tech Expo

ስካይ ሊንክ ቴክኖሎጂስ የመጀመሪያውን ዓመታዊ የጉዞ መርሐ ግብር አካሔደ።

ስካይ ሊንክ ቴክኖሎጂስ የመጀመሪያውን ዓመታዊ የጉዞ መርሐ ግብር አካሔደ።

Category: Events

ስካይ ሊንክ ቴክኖሎጂስ የመጀመሪያውን ዓመታዊ የጉዞ መርሐ ግብር አካሔደ።

ስካይሊንክ ቴክኖሎጂስ የቤተሰብ ዓመታዊ የጉዞ መርሐ ግብሩን ያካሔደው ትላንት ሰኞ መስከረም 5/2018 ነው።
በያያ ቪሌጅ የተካሔደው ልዩ መርሐ ግብር፤ ዓመቱን በሥራ ያሳለፉ የስካይ ሊንክ ሠራተኞች የታደሙበት እና የተዝናኑበት ሆኖ አልፏል።

ደማቅ በነበረው የተዝናኖት ቆይታ የተለያዩ ዝግጅቶች የነበሩ ሲሆን፤ በተለይም በዓመቱ የላቀ የሥራ አፈፃፀም በማስመዝገብ ለተመረጡ ኮከብ ሠራተኞች ዕውቅና እና ምስጋና የተቸረበት ሆኖ አልፏል።

በዚህም የተቋሙን ዓመታዊ የላቀ የሥራ አፈጻጸም በማሸነፍና የዓመቱ ምርጥ ሠራተኛ በመሆን፤ የSoftware Department ኃላፊው አቶ ሙሐመድ ዑመር የተመረጡ ሲሆን፤ ያስመዘገቡትን ውጤት ምክንያት በማድረግ የዘመናዊ ታብሌት ስጦታና የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በመርሐ ግብሩ ላይ ለስካይሊንክ ቤተሰቦች መልዕክታቸውን ያቀረቡት የስካይ ሊንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሙሐመድከረም አህመድ፤ "የዓመታዊ ጉዞው ዋነኛ ዓላማ ያሳለፍነውን የ2017 ዘመን በትጋት ተወጥተን፣ አዲሱን 2018 በተሻለ አፈጻፀም ለማሳለፍ አዲስ ኃይል የምንሞላበት ነው" ያሉ ሲሆን፤ "ለዓመቱ ኮከብ ሠራተኞች ያበረክትነው ሽልማትና፣ የሰጠነው ዕውቅና ለቀጣይ ሥራ የሚያተጋን እንደሆነ እምነታችን ነው” ሲሉ ገልጸዋል።

መልከ ብዙ የቴክኖሎጂ ሲስተምና ሥርዓቶችን በማበልጸግና ለበርካታ ችግሮች ቴክኖሎጂያዊ መፍትሄዎችን በማስተዋቅ አራት ዓመታትን የተሻገረው ስካይ ሊንክ ቴክኖሎጂስ፤ ለቀላልና ዘመናዊ ሕይወት እየተጋ የሚገኝ ተቋም መሆኑ ይታወቃል።

Subscribe for our latest update