International Tech Expo
የስትራይድ ኢትዮጵያ 2024 ኤክስፖ
Category: Events
ተቋማት "ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025" እውን አንዲሆን የበኩላቸውን ሚና እየተወጡ መሆኑን ተናገሩ፡፡
የስትራይድ ኢትዮጵያ 2024 ኤክስፖ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በይፋ መከፈቱ ይታወቃል።
ዓመታዊው ኤክስፖው "ሳይንስ በር ይከፍታል ቴክኖሎጂ ያስተሳስራል፤ ፈጠራ ወደ ፊት ያራምዳል" በሚል መሪ ሃሳብ በሳይንስ ሙዚየም እስከ ግንቦት 18/2016 ዓ.ም ለህዝብ ዕይታ ክፍት ሆኖ ይቆያል። ትኩረቱን ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራና ዲጂታላይዜሽን ላይ ያደረገው ስትራይድ ኢትዮጵያ ኤክስፖ በርካታ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ተቋማት ምርትና አገልግሎታቸውን አቅርበዋል።
የ "ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025" ስትራቴጂ በዋናነት የዲጂታል መሰረተ ልማት በመገንባት እና በማስፋት የአገሪቱን ምጣኔ ኃብታዊ፣ ማሕበራዊና ፖለቲካዊ እድገት ማፋጠንን ዓላማ ያደረገ ነው፡፡ በኤክስፖው የተሳተፉ አስተያየት ሰጪዎች የአገልግሎት አሰጣጥ እና አሰራሮችን በመፍጠር ለዲጂታል ኢትዮጵያ መሳካት የበኩላቸውን እየተወጡ መሆኑን ተናግረዋል።
አቶ መሐመድከረም አህመድ የስካይ ሊንክ ቴክኖሎጂሰእ መስራች ሲሆኑ ድርጅታቸው በኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ላይ የተሰማራ መሆኑን ገልጸዋል። ድርጅቱ ሶፍትዌር ማልማት፣ የአይቲ አስተዳደር፣ ዳታ ሴኪዩሪቲና የድረ-ገጽ ዲዛይን አገልግሎቶች ላይ መሰማራቱን ተናግረዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ የላቀ የአይቲ እውቀት ለድርጅቶችና ለትምህርት ተቋማት የሚሰጥ ሲሆን በተጨማሪም ወጣቶችን በቴክኖሎጂ የማብቃት ስራ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። ኢዜአ