+251-974-967171 | +251-936-177777
A.A, Bole Tropical Mall No. 217
Service Active Ethiopia Flag

International Tech Expo

በድሬዳዋ ከተማ ተዘጋጅቶ የነበረውን ምርኩዝ 30 የረመዳን ቀለማት 6 ልዩ መድረክ በፕላቲኒየም ደረጃ ስፖንሰር....

በድሬዳዋ ከተማ ተዘጋጅቶ የነበረውን ምርኩዝ 30 የረመዳን ቀለማት 6 ልዩ መድረክ በፕላቲኒየም ደረጃ ስፖንሰር....

Category: Events

ድርጅታችን ስካይ ሊንክ ቴክኖሎጂስ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር ዕለተ እሁድ የካቲት 16/2017 በድሬዳዋ ከተማ ተዘጋጅቶ የነበረውን ምርኩዝ 30 የረመዳን ቀለማት 6 ልዩ መድረክ በፕላቲኒየም ደረጃ ስፖንሰር በማድረግ፤ ለመላው የድሬዳዋ ከተማ እስልምና ኃይማኖት ተከታዮች እንኳን ለታላቁ የረመዳን ወር በሰላም አደረሳችሁ የሚል ልባዊ ምኞቱን ማስተላለፉ ይታወሳል።
በዚህ ከድሬዳዋ ከተማና በዙሪያዋ ከሚገኙ አጎራባች አካባቢዎች በርካታ ታዳሚያን በንቃት በተሳተፉበት ልዩ የረመዳን መቀበያ ዝግጅት፤ ድርጅታችን እንደ መድረኩ አጋር ተቋምነቱ አዘጋጅቶት በነበረው አሳታፊ የመድረክ ውድድር አሸናፊ ለሆኑ ታዳሚያን በየደረጃቸው የታብሌት፣ የስማርት ዎች እና የገንዘብ ሽልማት ማስረከብ ችሏል።
በዚህ አጋጣሚ ለድሬዳዋ ከተማ ነዋሪዎች የታላቁን የረመዳንን ወር አቀባበል ለማድመቅ በተሰናዳውና ስኬታማ በነበረው የምርኩዝ 30 መድረክ በፕላቲኒየም ደረጃ የዝግጅቱ አጋር በመሆናችን ልባዊ ደስታና ኩራት እንደሚሰማን ለመግለፅ እንወዳለን!!
ስካይ ሊንክ ቴክኖሎጂስ!
ለቀላልና ዘመናዊ ህይወት!

Subscribe for our latest update