International Tech Expo
የእንኳን ለ5ተኛ ዓመት አደረሳችሁ መልዕክት ለሚንበር ቲቪ ( Minber TV / ሚንበር ቲቪ )!
Category: News
የእንኳን ለ5ተኛ ዓመት አደረሳችሁ መልዕክት ለሚንበር ቲቪ ( Minber TV / ሚንበር ቲቪ )!
“ሁለንተናዊ ከፍታ” ላይ የመድረስ ራዕይ በመሰነቅ የሚንቀሳቀሰው ሚንበር ቲቪ ከተመሠረተ 5ተኛ ዓመቱን እያከበረ ይገኛል። በእነዚህ ዓመታት ውስጥ ጣቢያው በዋነኛነት በሳተላይት እንዲሁም ዘመን በደረሰበት የዲጂታል አማራጭ ሁሉ ወደ ውድ ተመልካቾቹ ሲደርስ ቆይቷል፡፡ በዚህም እንደ ጣቢያ ይዞት ከተነሳው ራዕይና ሊደርስበት ከሚናፍቀው ከፍታ ለመድረስ እየተጋ ይገኛል።
ከምስረታው ጀምሮ እኛም ቴሌቭዥን ጣቢያውን በቴክኖሎጂ ዘርፍ የጀርባ አጥንት በመሆን እንዲሁም ስፖንሰር በማድረግ አብረን እየሰራን ቆይተናል። ዛሬም አብሮ በመስራት ላይ እንገኛለን።
ድርጅታችን የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ለሰፊው ሕዝብ ለማድረስ ጣቢያውን ቀዳሚ ምርጫ በማድረጋችን በርካቶች ጋር በቀላሉ እንድንደርስ ሆኗል።
በቆይታችሁም በሚሊዮኖች ቤት ደረጃውን በጠበቀና ያለምንም መቆራረጥ መድረስ ችላችሃል፡፡ በዲጂታል አማራጮችም ሌሎች በርካታ ሚሊዮኖች ጋር ተደራሽ ሁናችኃል፡፡
በነኚህ የተወደዱና በተዋቡ ጊዜያት ለነበረን ውብ ቆይታ ከልብ እናመሰግናለን።
ውድ የሥራ አስፈፃሚ አባላት፣ ውድ ሠራተኞችና ወዳጅ ተመልካቾች በሙሉ እንኳን ለሚንበር ቲቪ 5ኛ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ እያልኩ፤ ቀጣዮቹም ዓመታት ይበልጥ በተሻለ ሁለንተናዊ ከፍታ እንደምትመጡ መልካም ምኞቴን በድርጅታችን ስም እየገለፅኩ ወደፊትም በሚያስፈልጉ የቴክኖሎጂ እገዛዎች ላይ ከጎናችሁ መሆናችን ለመግለፅ እወዳለው።
©አቶ መሀመድከረም አህመድ
(የስካይሊንክ ቴክኖሎጂ ዋና ሥራ አስፈፃሚ)