International Tech Expo
የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ኤክስፖ ከከግንቦት 8 እስከ 10፣2017 ድረስ በአዲስ ኮንቬንሽን ማዕከል ይካሄዳል።
Category: Events
የአፍሪካ የኢትዮጵያ ዲጂታላይዜሽን መጻኢ ጉዞ የሚዳሰስበት የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ኤክስፖ ከከግንቦት 8 እስከ 10፣2017 ድረስ በአዲስ ኮንቬንሽን ማዕከል ይካሄዳል።
የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ኤክስፖ (ETEX 2025) ኢትዮጵያ የደረሰችበትን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ለዓለማቀፉ ማሕበረሰብ የምታሳይበት ትልቅ መድረክ ነዉ።
ኤክስፖዉ በሚኖረዉ ቆይታ የቴክኖሎጂዉን ሥነ ምህዳር ማስፋት ብሎም በዘርፉ ትብብር ማድረግ በሚቻልበት ዐውድ ዙሪያ ዉይይቶች ይካሄዳሉ።
በሁነቱ የመጀመሪያ ቀን ውሎ የሳይበር ደህንነት መሠረተ ልማት፣ ጥበቃ እንዲሁም በዘርፉ ሊቀረፉ ስለሚገባቸዉ ችግሮች ጥልቅ ዉይይቶች ይኖራሉ።
በሁለተኛዉ ቀን አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የአፍሪካን የዲጂታላይዜሽን ጉዞ ለማሳካት ያለዉን አስተዋጽኦ የሚያመላክቱ ዉይይቶች ይካሄዳሉ። የኤክስፖዉ ተሳታፊ በሆኑ ዓለማቀፍ የዘርፉ ባለድርሻዎች መካከል የልምድ ልዉዉጦችም ይደረጋሉ፡፡