International Tech Expo
Google ከplaystore ውጪ በሚጫኑ መተግበሪያዎች ላይ የdeveloper verification ሊጠይቅ ነው።
Category: News
Google ከplaystore ውጪ በሚጫኑ መተግበሪያዎች ላይ የdeveloper verification ሊጠይቅ ነው።
Google የአንድሮይድ አፕሊኬሽኖችን ስርጭት የደህንነት እያጠናከረ መሆኑን ሰኞ ዕለት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
ድርጅቱ እንደገለፀው ከሆነ ከቀጣይ አመት ጀምሮ ከPlaystore ውጭ የሚጫኑ መተግበሪያቸውን የሚሰሩ ዲቨሎፐሮችን ማንነት ማረጋገጥ እንደሚጀምር አስታውቋል።
ግዙፉ የቴክኖሎጂው ድርጅት እንዳስታወቀው የአፕሊኬሽን አበልፃጊዎች ከፕሌይስቶር ውጭ በሌሎች አፕሊኬሽን ስቶሮች ማሰራጨት አይችሉም ማለት አይደለም። ነገር ግን ማንነታቸውን በመደበቅ የተለያዩ ቫይረስና ማልዌሮችን የሚያሰራጩ፣ የግለሰቦችን መረጃ የሚሰበስቡትን እንዲሁም የፋይናንስ ወንጀል የሚፈፅሙትን ለመቆጣጠር ግዴታ ማንነታቸውን ማጣራት ግድ ይሆናል ብሏል።
በማንነት ማጣራቱ ላይ አንድ developer ህጋዊ ስሙን፣ የመኖሪያ አድራሻውን፣ ኢሜይል አድራሻውንና ስልክ ቁጥሩን፣ የመንግስት መታወቂያውን እንዲሁም ሌሎች ዝርዝር የግል መረጃዎቹን ማቅረብ እና ማረጋገጥ ይጠበቅበታል።
እንደ ድርጅት የተመዘገበ ከሆነ የD-U-N-S ቁጥርና የድርጅቱን ድረ-ገጽ ማረጋገጥ ይኖርበታል።
Google አጠናሁት ባለው ጥናት መሰረት ከPlaystore ውጪ የሚጫኑ አፕሊኬሽኖች 50 እጥፍ ለማልዌርና ለቫይረሶች ተጋላጭ እንደሆኑ ይፋ አድርጓል።
ከኦክቶበር 2025 ጀምሮ ፍላጎት ያላቸው ዴቨሎፐሮች ሲስተሙን ለመፈተሽና feedback ለመስጠት መመዝገብ የሚችሉ ሲሆን ከmarch 2026 ጀምሮ ለሁሉም ክፍት ይሆናል።
ከ2027 ጀምሮ በአለም አቀፍ ደረጃ ተግባራዊ እንደሚደረግ የሚጠበቅ ሲሆን ይህም የአንድሮይድ ተጠቅቃሚዎችን ደህንነት ሊጨምር ይችላል ተብሏል።
ᵇⁱᵍʰᵃᵇᵉˢʰᵃ
#skylink #tech #ai #google #techsolution