+251-974-967171 | +251-936-177777
A.A, Bole Tropical Mall No. 217
Service Active Ethiopia Flag

International Tech Expo

‼️ለ Windows 10 የሚቀርቡ ወሳኝ ማሻሻያዎች ከ28 ቀናት በኋላ ይቋረጣሉ::

‼️ለ Windows 10 የሚቀርቡ ወሳኝ ማሻሻያዎች ከ28 ቀናት በኋላ ይቋረጣሉ::

Category: News

‼️ለ Windows 10 የሚቀርቡ ወሳኝ ማሻሻያዎች ከ28 ቀናት በኋላ ይቋረጣሉ::

ማይክሮሶፍት ኩባንያ ከመጪዉ ጥቅምት 4/2018 ዓ.ም (October 14, 2025) በኋላ ለwindows10 ምርቶች የሚያቀርበዉን ወሳኝ የሆኑ ማሻሻያዎች እንደማያቀርብ በድጋሚ ለደንበኖቹ አሳዉቋል።

ለwindows10 የደህንነት ማሻሻያ ሲቋረጥ፤ ከwondows 10 ምርት ከዚህ ቀደም በየወሩ የሚያገኙት ደህንነትን (security)፣ የሲስተም መረጋጋትን (stability) ወይም ከአጠቃቀም ጋር ለሚፈጠሩ ክፍተቶች ጥገናዎችን ወይም ቴክኒካል ድጋፍን መስጠት ያቆማል።

በጥቅምት 4/ 2018 ዓ.ም (October 14, 2025) በኋላም የwindows 10 ስሪት 22H2 (Home፣ Pro፣ Enterprise፣ Education፣ እና IoT Enterprise እትሞች) በሙሉ የአገልግሎታቸዉ እንደሚያበቃ ታዉቋል።

ማይክሮሶፍት እነዚህ የዊንዶዉስ-10 ምርት ተጠቃሚዎች ወሳኝ የሆኑ የደህንነት ዝመናዎችን በቀጣይነት ለማግኘት የዊንዶዉስ ምርታቸዉን ወደ Windows11 እንዲያሳድጉ መክሯል።

ነገር ግን የWindows10 የደህንነት ማሻሻያዎች እንዳይቋረጥ የሚፈልጉ ተጠቃሚዎች ለዊንዶዉስ ሆም (Home) ተጠቃሚዎች 30 የአሜሪካን ዶላር እንዲሁም ለኢንተርፕራይዝ (Enterprise) ተጠቃሚዎች ደግሞ ለእያንዳንዱ መሳሪያ በአመት 61 የአሜሪካ ዶላር በመክፈል ወርሃዊ ዝመናዎችን ማስቀጠል እንደሚችሉ አሳዉቋል።

በመሆኑም የwindows10 ተጠቃሚዎች ጊዜዉ ከማለፉ በፊት የምትጠቀሙበትን የwindows ምርትን ወደ Windows11 ከፍ በማድረግ የደህንነት ማሻሻያዎች መቋረጠቻዉን ተከትሎ በሳይበር ጥቃት ተገላጭነት ሊደርስ የሚችለዉን አደጋ እንድትከላከሉ ለማሳወቅ እንወዳለን።

#technews #techtips #skylink #windows10

Subscribe for our latest update